እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፤ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች ዕወቁ፤ በእርስዋም ላይ ሂዱ፤ ለነፍሳችሁም መድኀኒትን ታገኛላችሁ፤” እነርሱ ግን፥ “አንሄድባትም” አሉ።
ሉቃስ 5:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከረመውን የወይን ጠጅ ሊጠጣ ወድዶ አዲሱን የሚሻ የለም፤ የከረመው ይሻላል ይላልና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ፣ አሮጌ የወይን ጠጅ ከጠጣ በኋላ፣ አዲሱን የሚሻ ማንም የለም፤ ምክንያቱም፣ ‘አሮጌው የተሻለ ነው’ ስለሚል ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም አሮጌውን የወይን ጠጅ ከጠጣ በኋላ አዲሱን የሚሻ የለም፤ ‘አሮጌው ይጣፍጣል’ ይላልና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ጊዜ የቈየ ደረቅ የወይን ጠጅ የጠጣ አዲሱን በተሐ የወይን ጠጅ መጠጣት አይፈልግም፤ ‘የቈየው ደረቅ የወይን ጠጅ የተሻለ ነው፥’ ይላልና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮጌ የወይን ጠጅ ሲጠጣ አዲሱን የሚሻ ማንም የለም፤ አሮጌው ይጣፍጣል ይላልና። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፤ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች ዕወቁ፤ በእርስዋም ላይ ሂዱ፤ ለነፍሳችሁም መድኀኒትን ታገኛላችሁ፤” እነርሱ ግን፥ “አንሄድባትም” አሉ።
ከዚህም በኋላ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ በሰንበት ቀን በእርሻ መካከል ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም እሸት ቈርጠው በእጃቸው እያሹ በሉ።