ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።
ሉቃስ 5:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ሰዎች በአልጋ ተሸክመው ሽባ የሆነ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፤ እንዲፈውሰውም ወደ እርሱ ሊያስገቡት ወደዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜም፣ ሰዎች አንድ ሽባ በቃሬዛ ተሸክመው አመጡ፤ ኢየሱስ ፊት ለማኖርም ወደ ቤት ሊያስገቡት ሞከሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆም፥ አንድ መንቀሳቀስ የማይችል ሰው በአልጋ ተሸክመው አመጡ፤ አስገብተውትም በፊቱ ሊያኖሩት ይፈልጉ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ አንድ ሽባ ሰው በአልጋ የተሸከሙ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጡ፤ ኢየሱስ ወደ ነበረበት ቤትም አግብተው በፊቱ ሊያኖሩት ፈልገው ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ አንድ ሽባ በአልጋ ተሸክመው አመጡ፤ አግብተውም በፊቱ ሊያኖሩት ይሹ ነበር። |
ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።
ለሰው ልጅ በምድር ላይ ኀጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፤ ያን ሽባ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ ብዬሃለሁ” አለው።