በገሊላ ምኲራቦችም ይሰብክ ነበር።
በይሁዳም በምኵራቦች መስበኩን ቀጠለ።
እርሱም በይሁዳ በሚገኙት ምኵራቦች ይሰብክ ነበር።
ስለዚህ በይሁዳም ምኲራቦች ሁሉ እየተዘዋወረ ይሰብክ ነበር።
በገሊላም ምኵራቦች ይሰብክ ነበር።
ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።
በምኵራባቸውም እየሰበከ አጋንንትንም እያወጣ ወደ ገሊላ ሁሉ መጣ።
በየምኵራባቸውም ሁሉ ያስተምራቸው ነበር፤ ትምህርቱንም ያደንቁ ነበር፤ ሁሉም ያመሰግኑት ነበር።
ብዙ ሰዎችም በእርሱ ዘንድ ነበሩ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ይሰሙ ነበር፤ እርሱ ግን በጌንሴሬጥ ባሕር ወደብ ቁሞ ነበር።