ሉቃስ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዲያብሎስም፥ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህስ ይህ ድንጋይ እንጀራ ይሁን በል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዲያብሎስም፣ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ ይህን ድንጋይ እንጀራ እንዲሆን እዘዘው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዲያብሎስም፦ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ ይህን ድንጋይ እንጀራ እንዲሆን እዘዝ፤” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዲያብሎስም ኢየሱስን፦ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እስቲ ይህን ድንጋይ እንጀራ እንዲሆን እዘዝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዲያብሎስም፦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ ይህን ድንጋይ፦ እንጀራ ሁን ብለህ እዘዝ አለው። |
መንፈስ ቅዱስም የርግብ መልክ ባለው አካል አምሳል በእርሱ ላይ ወረደ፤ ከሰማይም፥ “የምወድህ፥ በአንተም ደስ የሚለኝ ልጄ አንተ ነህ” የሚል ቃል መጣ። ሉቃ. 9፥35።
አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት ከዲያብሎስ ተፈተነ፥ በእነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፤ እነዚያም ቀኖች ከተፈጸሙ በኋላ ተራበ።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ሰው የሚኖረው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ነው እንጂ በእንጀራ ብቻ አይደለም የሚል ተጽፎአል” አለው።