La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 4:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኤል​ያስ የሲ​ዶና ክፍል በም​ት​ሆን በስ​ራ​ጵታ ወደ​ም​ት​ኖር ወደ አን​ዲት መበ​ለት ሴት እንጂ ከእ​ነ​ዚህ ወደ አን​ዲቱ እን​ኳን አል​ተ​ላ​ከም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኤልያስ ከእነዚህ መካከል ወደ አንዷም አልተላከም፤ ነገር ግን በሲዶና አገር በሰራፕታ ወደ ነበረችው መበለት ተላከ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ቢሆንም ግን ኤልያስ ወደ ሲዶናዊቷ መበለት ወደ ሰራፕታ እንጂ ወደ ሌሎቹ ወደ አንዳቸውም አልተላከም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ኤልያስ፥ በሲዶና አገር ሰራጵታ በምትባል መንደር ወደምትገኘው ወደ አንዲት ባልዋ የሞተባት ሴት ብቻ ተላከ እንጂ ወደ ሌላ ወደ ማንም አልተላከም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኤልያስም በሲዶና አገር ወዳለች ወደ ሰራፕታ ወደ አንዲት መበለት እንጂ ከእነርሱ ወደ አንዲቱ አልተላከም።

Ver Capítulo



ሉቃስ 4:26
3 Referencias Cruzadas  

ይህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የጭ​ፍ​ራ​ቸው ምርኮ የከ​ነ​ዓ​ንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራ​ጵታ ድረስ ይወ​ር​ሳል፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምር​ኮ​ኞች እስከ ኤፍ​ራታ ድረስ የደ​ቡ​ብን ከተ​ሞች ይወ​ር​ሳሉ።


“ወዮልሽ ኮራዚ! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና።