La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 21:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ር​ሱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህ መቼ ይደ​ረ​ጋል? ይህስ የሚ​ሆ​ን​በት ጊዜው፥ ምል​ክ​ቱስ ምን​ድን ነው?” ብለው ጠየ​ቁት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም፣ “መምህር ሆይ፤ እንግዲህ ይህ ሁሉ የሚሆነው መቼ ነው? ደግሞም ይህ እንደሚሆን ምልክቱ ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም “መምህር ሆይ! እንግዲህ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ሊሆን መቃረቡን የሚያሳየው ምልክቱ ምንድነው?” ብለው ጠየቁት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም “መምህር ሆይ! ይህ የሚሆነው መቼ ነው? ይህስ የሚሆንበት ጊዜ መቃረቡን የምናውቅበት ምልክት ምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም፦ መምህር ሆይ፥ እንግዲህ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ይሆን ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው? ብለው ጠየቁት።

Ver Capítulo



ሉቃስ 21:7
13 Referencias Cruzadas  

እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው “ንገረን፤ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው?” አሉት።


“ነገር ግን በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፤ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤


እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይህ ሁሉ እስ​ኪ​ደ​ረግ ድረስ ይህቺ ትው​ልድ አታ​ል​ፍም።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ይህን ታያ​ላ​ች​ሁን? በእ​ዚህ ቦታ ድን​ጋይ በድ​ን​ጋይ ላይ የማ​ይ​ተ​ው​በ​ትና ሳይ​ፈ​ርስ የማ​ይ​ቀ​ር​በት ዘመን ይመ​ጣል።”


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ብዙ​ዎች እኔ ክር​ስ​ቶስ ነኝ፤ ጊዜ​ውም ደር​ሶ​አል እያሉ በስሜ ይመ​ጣ​ሉና እን​ዳ​ያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ተከ​ት​ላ​ችሁ አት​ሂዱ።