La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 20:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ብለው ጠየ​ቁት፥ “መም​ህር ሆይ፥ ሙሴ፦ ‘ወን​ድሙ ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሚስ​ቱን ትቶ የሞ​ተ​በት ሰው ቢኖር ወን​ድሙ ሚስ​ቱን አግ​ብቶ ለወ​ን​ድሙ ዘር ይተካ’ ሲል ጽፎ​ል​ናል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህም አሉት፤ “መምህር ሆይ፤ አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፣ ወንድሙ የሟችን ሚስት አግብቶ ልጆች በመውለድ ለወንድሙ ዘር እንዲተካ ሙሴ ጽፎልናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም አሉ፤ “መምህር ሆይ! ሙሴ ‘አንድ ሰው ባለትዳር ወንድም ቢኖረውና፥ እርሱም ሳይወልድ ቢሞት፥ ወንድሙ የእርሱን ሚስት አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ፤’ ብሎ ጻፈልን።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“መምህር ሆይ! ሙሴ እንዲህ ሲል ጽፎልናል፤ ‘አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ከሚስቱ በሞት ቢለይ ወንድሙ ሴትዮዋን አግብቶ ለሟቹ ዘር ያትርፍለት።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህ ሲሉ፦ መምህር ሆይ፥ ሙሴ፦ ሚስት ያለችው የአንድ ሰው ወንድም ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥ ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ ብሎ ጻፈልን።

Ver Capítulo



ሉቃስ 20:28
6 Referencias Cruzadas  

ይሁ​ዳም ምራ​ቱን ትዕ​ማ​ርን፥ “ልጄ ሴሎም እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በአ​ባ​ትሽ ቤት መበ​ለት ሆነሽ ተቀ​መጪ” አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወን​ድ​ሞቹ እን​ዳ​ይ​ሞ​ት​ብኝ ብሎ​አ​ልና። ትዕ​ማ​ርም ሄዳ በአ​ባቷ ቤት ተቀ​መ​ጠች።


ይሁ​ዳም አይቶ “ከእኔ ይልቅ ትዕ​ማር እው​ነ​ተኛ ሆነች፤ ልጄን ሴሎ​ምን አል​ሰ​ጠ​ኋ​ት​ምና” አለ። ትገ​ደል ማለ​ት​ንም ተወ፤ ደግ​ሞም አላ​ወ​ቃ​ትም።


ይሁ​ዳም አው​ና​ንን፥ “ወደ ወን​ድ​ምህ ሚስት ግባ፤ አግ​ባ​ትም፤ ለወ​ን​ድ​ም​ህም ዘርን አቁ​ም​ለት” አለው።


እን​ግ​ዲህ ከእኛ ዘንድ ሰባት ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ነበሩ፤ ታላቁ ሚስት አግ​ብቶ ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሞተ።