ሉቃስ 2:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ደግሞ ተቀብሎ በክንዱ ታቀፈው፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስምዖን ተቀብሎ ዐቀፈው፤ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እንዲህ አለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ደግሞ ተቀብሎ አቀፈው፤ እግዚአብሔርንም እየባረከ እንዲህ አለ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስምዖን ሕፃኑን ተቀብሎ ዐቅፎ፥ እግዚአብሔርን በማመስገን እንዲህ አለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ደግሞ ተቀብሎ አቀፈው እግዚአብሔርንም እየባረከ እንዲህ አለ፦ |
መንፈስም ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደው፤ ዘመዶቹም በሕግ የተጻፈውን ያደርጉለት ዘንድ ሕፃኑን ጌታችን ኢየሱስን ወደ ቤተ መቅደስ በአገቡት ጊዜ፥
ነገሩም የእስራኤልን ልጆች ደስ አሰኘ፤ ለእስራኤልም ልጆች በነገሩአቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ የተቀመጡባትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ለመውጋት አንወጣም ተባባሉ።