ሉቃስ 19:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምን ገንዘቤን ወደ ለዋጮች አላስገባህም? እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር በወሰድሁት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጥቼ ገንዘቤን ከነትርፉ እንድወስድ፣ ለምን ለሚሠሩበት ሰዎች አልሰጠህም?’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታዲያ ገንዘቤን ለገንዘብ ለዋጮች አደራ ያልሰጠኸው ለምንድን ነው? እኔም መጥቼ ከነትርፉ እወስደው ነበር፤’ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ ገንዘቤን ትርፍ በሚያስገኝልኝ በባንክ ለምን አላስቀመጥከውም ነበር? እኔ ተመልሼ ስመጣ ከነትርፉ እወስደው ነበር’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር አለው። |
ጌታውም እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉ ሰነፍ አገልጋይ፥ እኔ ያላስቀመጥሁትን የምወስድ፥ ያልዘራሁትን የማጭድ፥ ያልበተንሁትንም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? እንደ ቃልህ እፈርድብሃለሁ።