ሉቃስ 18:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚመሩትም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን በጣም ጮኾ፥ “የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፊት የሚሄዱ ሰዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፣ “የዳዊት ልጅ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ የባሰ ጮኸ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስተ ፊት ይሄዱ የነበሩትም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረኝ፤” እያለ አብዝቶ ጮኸ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀድመው እፊት እፊት ይሄዱ የነበሩት ሰዎች፦ “ዝም በል!” ብለው ገሠጹት። እርሱ ግን ድምፁን በይበልጥ ከፍ አድርጎ፦ “የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረኝ!” ይል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስተ ፊት ይሄዱ የነበሩትም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፦ የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ። |
እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! የጽድቅንና የዕውቀትን መክፈቻ ወስዳችሁ ትሰውራላችሁና፤ እናንተም አትገቡምና፤ የሚገቡትንም መግባትን ትከለክሉአቸዋላችሁ።”