ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።
ሉቃስ 18:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥራ ሁለቱንም ወሰዳቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ በነቢያትም የተጻፈው ሁሉ በሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻ ወስዶ እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ ነቢያት ስለ ሰው ልጅ የጻፉትም ሁሉ ይፈጸማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው “እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ ስለ ሰው ልጅም በነቢያት የተጻፈው ሁሉ ይፈጸማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ! ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ ስለ ሰው ልጅ በነቢያት የተጻፈው ሁሉ በዚያ ይፈጸማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ ስለ ሰው ልጅም በነቢያት የተጻፈው ሁሉ ይፈጸማል። |
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።
ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ይወርድ ነበር፤ ሽፍቶችም አገኙት፤ ደበደቡት፥ አቈሰሉት፥ ልብሱንም ገፍፈው፤ በሕይወትና በሞት መካከል ጥለውት ሄዱ።
“ለሰው ልጅ ብዙ መከራ ያጸኑበት ዘንድ ሽማግሌዎችና የካህናት አለቆች፥ ጻፎችም ይፈትኑት ዘንድ፥ ይገድሉትም ዘንድ፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ አለው” አላቸው።