La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 18:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት እንደ ሕፃ​ናት ያል​ተ​ቀ​በ​ላት አይ​ገ​ባ​ባ​ትም።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበል ሁሉ ከቶ አይገባባትም።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም፤” አለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በእውነት እላችኋለሁ! የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን ያልተቀበላት ሰው አይገባባትም።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እውነት እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም አለ።

Ver Capítulo



ሉቃስ 18:17
8 Referencias Cruzadas  

እንዲህም አለ “እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።


ነገር ግን ኢየሱስ “ሕፃናትን ተዉአቸው፤ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና” አለ፤


እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም፤” አላቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጠራ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ሕፃ​ና​ትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉ​አ​ቸው፥ አት​ከ​ል​ክ​ሉ​አ​ቸ​ውም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እንደ እነ​ዚህ ላሉት ናትና።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በአ​እ​ምሮ እንደ ሕፃ​ናት አት​ሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃ​ናት ሁኑ፤ በዕ​ው​ቀ​ትም ፍጹ​ማን ሁኑ።


እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።


ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።