ጌታችን ኢየሱስም ጠራቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉአቸው፥ አትከልክሉአቸውም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና።
ሉቃስ 18:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይባርካቸውም ዘንድ ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡአቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም አይተው ገሠጹአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ እንዲዳስሳቸው ሰዎች ሕፃናትን ወደ እርሱ ያመጡ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም ይህን ባዩ ጊዜ ገሠጿቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ደግሞ ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም አይተው ገሠጹአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ እንዲዳስሳቸው ሰዎች ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱ ይህን ባዩ ጊዜ ሰዎቹን ተቈጡአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ደግሞ ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም አይተው ገሠጹአቸው። |
ጌታችን ኢየሱስም ጠራቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉአቸው፥ አትከልክሉአቸውም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና።
ደቀ መዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስም ይህን ባዩ ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ኤልያስ እንደ አደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንድንል ትፈቅዳለህን?” አሉት።
እርስዋም ከእርሱ ጋር አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፥ እንጀራ፥ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወጣች። በሴሎም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት ገባች። ልጃቸውም ከእነርሱ ጋር ነበረ።
በእግዚአብሔርም ፊት አቀረቡት ፤ አባቱም በየዓመቱ ለእግዚአብሔር የሚሠዋውን መሥዋዕት ሠዋ። ሕፃኑንም አቀረበው፤ ወይፈኑንም አረደ፤ እናቱም ሐና ሕፃኑን ወደ ዔሊ አገባችው።