ሉቃስ 17:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐዋርያትም ጌታን፥ “እምነትን ጨምርልን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐዋርያትም ጌታን፣ “እምነታችንን ጨምርልን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐዋርያትም ጌታን “እምነት ጨምርልን” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐዋርያቱም ጌታ ኢየሱስን “እባክህ እምነት ጨምርልን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐዋርያትም ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት። |
ዮሐንስም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ጠርቶ፥ “የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ተስፋ የምናደርገው ሌላ አለ?” ብሎ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ላካቸው።
ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ፥ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤
የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ፥ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።