ሉቃስ 16:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘እነሆ፥ ደብዳቤህ፤ ተቀምጠህ አምሳ ማድጋ አለብኝ ብለህ ፈጥነህ ጻፍ’ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እርሱም፣ ‘አንድ መቶ ማድጋ ዘይት አለብኝ’ አለ። “መጋቢውም፣ ‘የውል ወረቀትህን ዕንካ፤ ቶሎ ተቀምጠህ “ዐምሳ ማድጋ” ብለህ ጻፍ’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ‘መቶ ማድጋ ዘይት’ አለ። ‘የጽሑፍ ማስረጃህን እንካ፥ ፈጥነህም ተቀምጠና ኀምሳ ብለህ ጻፍ፤’ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ‘መቶ ማድጋ ዘይት ዕዳ አለብኝ’ አለ፤ መጋቢው ‘የፈረምከው ውል ይኸውልህ ቶሎ ተቀመጥና ኀምሳ ማድጋ ብለህ ጻፍ’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ መቶ ማድጋ ዘይት አለ። ደብዳቤህን እንካ ፈጥነህም ተቀምጠህ አምሳ ብለህ ጻፍ አለው። |
ለጌታውም ዕዳ የሚከፍሉትን ጠራቸው፤ የመጀመሪያውንም፦ ‘ለጌታዬ የምትከፍለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እርሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ዘይት ነው’ አለው።
ሁለተኛውንም፦ ‘አንተሳ ለጌታዬ የምትከፍለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እርሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ስንዴ ነው’ አለው፤ ‘እነሆ፥ ደብዳቤህ፤ ተቀምጠህ ሰማንያ አለብኝ ብለህ ፈጥነህ ጻፍ’ አለው።
እኔም እላችኋለሁ፦ ባለቀባችሁ ጊዜ እነርሱ በዘለዓለም ቤታቸው ይቀበሉአችሁ ዘንድ በዐመፃ ገንዘብ ለእናንተ ወዳጆች አድርጉበት።
በዚያም እንደ አይሁድ ልማድ የሚያነጹባቸው ስድስት የድንጋይ ጋኖች ነበሩ፤ ከእነርሱም እያንዳንዱ ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።