እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም ስለ ኀጢአታችን ለሞት አሳልፎ ሰጠው።
ሉቃስ 15:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእናንተ መካከል መቶ በጎች ያሉት ሰው ቢኖር፥ ከእነርሱ አንዲቱ ብትጠፋው ዘጠና ዘጠኙን በምድረ በዳ ትቶ እስኪያገኛት ድረስ ይፈልጋት ዘንድ ወደ ጠፋችው ይሄድ የለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከእናንተ መካከል አንዱ መቶ በጎች ቢኖሩትና ከእነርሱ አንዱ ቢጠፋበት፣ ዘጠና ዘጠኙን በሜዳ ላይ ጥሎ የጠፋውን እስኪያገኝ ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከእናንተ መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከእናንተ መካከል መቶ በግ ያለው ሰው ከመቶዎቹ አንድ በግ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በዱር ትቶ የጠፋውን እስኪያገኝ ድረስ ለመፈለግ የማይሄድ ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው? |
እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም ስለ ኀጢአታችን ለሞት አሳልፎ ሰጠው።
በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፥ በቆላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም ሀገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በጎቹ በተቈጣጣሪያቸው እጅ እንደ ገና ያልፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
“ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤ እረኞቻቸው አሳቱአቸው፤ በተራሮችም ላይ የተቅበዘበዙ አደረጉአቸው፤ ከተራራ ወደ ኮረብታ ዐለፉ፤ በረታቸውንም ረሱ።
የጠፋውንም እፈልጋለሁ፤ የባዘነውንም እመልሳለሁ፤ የተሰበረውንም እጠግናለሁ፤ የደከመውንም አጸናለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውንም እጠብቃለሁ፤ በፍርድም እጠብቃቸዋለሁ።”
የደከመውን አላጸናችሁትም፤ የታመመውንም አልፈወሳችሁትም፤ የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም፤ የባዘነውንም አልመለሳችሁትም፤ የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም፤ በኀይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረኞች ስለሌሉ፥ እረኞችም በጎችን ስላልፈለጉ፥ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎችን ስላላሰማሩ፥ በጎች ንጥቂያ ሆነዋልና፥ በጎችም ለዱር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና፤
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ አላቸው፥ “እናንት ግብዞች፥ እናንተሳ አህያችሁን ወይም በሬአችሁን በሰንበት ቀን ገለባ ከሚበላበት አትፈቱትምን? ውኃ ልታጠጡትስ አትወስዱትምን?
አንተ ሰው ሆይ፥ እውነት ለሚፈርደው ለእግዚአብሔር ምን ትመልስለታለህ? በወንድምህ ላይ የምትጠላውን ያን ሥራ አንተ ራስህ ከሠራኸው በራስህ የምትፈርድ አይደለምን? አንተ ራስህ ያን ሥራ ትሠራዋለህና።