ሉቃስ 12:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነት እላችኋለሁ፥ በሀብቱ ሁሉ ላይ ይሾመዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነት እላችኋለሁ፤ ባለው ንብረት ሁሉ ላይ ይሾመዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነት እላችኋለሁ፤ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነት እላችኋለሁ፤ ጌታው ያን አገልጋይ የንብረቱ ሁሉ ኀላፊ አድርጎ ይሾመዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል። |
ነገር ግን ያ ክፉ አገልጋይ በልቡ፦ ጌታዬ ቶሎ አይመጣም ቢል፥ በጌታው ቤት ያሉትንም ወንዶችንና ሴቶችን አገልጋዮች ሊደበድብና ሊያጕላላ ቢጀምር፥ ከሰካራሞችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥ ቢሰክርም፥
ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዐይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።