ሉቃስ 12:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም የምትበሉትንና የምትጠጡትን አትፈልጉ፤ ወዲያና ወዲህም አትበሉ፤ አትጨነቁለትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ምን እንደምትበሉና ምን እንደምትጠጡ አትሹ፤ አትጨነቁም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም የምትበሉትን የምትጠጡትንም አትፈልጉ፤ አታወላውሉም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ ‘ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን?’ እያላችሁ በማሰብ አትጨነቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም የምትበሉትን የምትጠጡትንም አትፈልጉ፥ አታወላውሉም፤ |
ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አላቸው፥ “ስለዚህ እላችህዋለሁ፤ ለነፍሳችሁ ስለምትበሉትና ስለምትጠጡት፥ ለሰውነታችሁም ስለምትለብሱት አትጨነቁ።
ደግሞም፥ “ያለ ስልቻ፥ ያለ ከረጢትና ያለ ጫማ በላክኋችሁ ጊዜ በውኑ የተቸገራችሁት ነገር ነበርን?” አላቸው፤ እነርሱም፥ “የለም” አሉት።