ሉቃስ 11:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! በምኵራብ ፊት ለፊት መቀመጥን፥ በገበያም እጅ መነሣትን ትወዳላችሁና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ፤ በምኵራብ የከበሬታ መቀመጫ፣ በገበያ ስፍራ የአክብሮት ሰላምታ ትወድዳላችሁና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! በምኵራቦች የከበሬታን ወንበርንና በገበያ ቦታዎች ሰላምታን ትወዳላችሁና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! በምኲራብ ውስጥ በክብር ወንበር ላይ መቀመጥ ትወዳላችሁ፤ እንዲሁም በአደባባይና በገበያ ቦታ ሰው ሁሉ እጅ እንዲነሣችሁ ትፈልጋላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ፈሪሳውያን፥ በምኵራብ የከበሬታ ወንበር በገበያም ሰላምታ ስለምትወዱ፥ ወዮላችሁ። |
“ልብሳቸውን አንዘርፍፈው ወዲያ ወዲህ ማለትን ከሚሹ፥ በገበያ እጅ መነሣትንና በአደባባይ ፊት ለፊት፥ በማዕድም ጊዜ በከበሬታ መቀመጫ መቀመጥን ከሚወዱ ጻፎች ተጠበቁ።
እርስ በርሳችሁ በወንድማማችነት መዋደድ ተዋደዱ፤ የምትራሩም ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤ መምህሮቻችሁንም አክብሩ።
በክርክርና ከንቱ ውዳሴን በመውደድ አትሥሩ፤ ትሕትናን በያዘ ልቡና ከራሳችሁ ይልቅ ባልንጀራችሁን አክብሩ እንጂ አትታበዩ።