ሉቃስ 11:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጣም ጊዜ ተጠርጎ አጊጦም ያገኘዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሲመለስም ቤቱ ጸድቶና ተዘጋጅቶ ያገኘዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲመጣም ተጠርጎና ተስተካክሎ ያገኘዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተመልሶ ሲመጣ ጸድቶና ተዘጋጅቶ ያገኘዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲመጣም ተጠርጎ አጊጦም ያገኘዋል። |
“ክፉ ጋኔንም ከሰው በወጣ ጊዜ ውኃ ወደሌለበት ምድረ በዳ ይሄዳል፤ የሚያርፍበትንም መኖሪያ ይሻል፤ ያላገኘ እንደ ሆነም ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል።
ከዚህም በኋላ ይሄድና ከእርሱ የሚከፉ ሌሎች ባልንጀሮቹን ሰባት አጋንንት ያመጣል፤ ገብተውም በዚያ ሰው ያድሩበታል፤ ለዚያ ሰውም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው የከፋ ይሆንበታል።”