ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፤
ሉቃስ 10:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር ሰላማችሁ ያድርበታል፤ ያለዚያ ግን ሰላማችሁ ይመለስላችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰላም ሰው በዚያ ካለ፣ ሰላማችሁ ያርፍበታል፤ አለዚያም ሰላማችሁ ለእናንተው ይመለሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር፥ ሰላማችሁ በእርሱ ላይ ያድርበታል፤ ካልሆነ ግን ይመለስላችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰላም ወዳድ ሰው በዚያ ቤት ቢኖር ሰላማችሁ ያድርበታል፤ አለበለዚያ ግን ሰላማችሁ ወደ እናንተ ይመለሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር፥ ሰላማችሁ ያድርበታል፤ አለዚያም ይመለስላችኋል። |
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፤
በከንቱ ነገርም የሚያስታችሁ አይኑር፤ በእርሱ ምክንያት በከሓዲዎች ልጆች ላይ የእግዚአብሔር መዓት ይመጣልና።
ስለዚህም በጌታችንና በቤቱ ሁላ ክፉ ነገር እንዲመጣ ተቈርጦአልና፥ እርሱ ክፉ ሰው ስለ ሆነ ማንም ሊናገረው አይችልምና የምታደርጊውን ተመልከቺና ዕወቂ።”