ሉቃስ 10:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ይወርድ ነበር፤ ሽፍቶችም አገኙት፤ ደበደቡት፥ አቈሰሉት፥ ልብሱንም ገፍፈው፤ በሕይወትና በሞት መካከል ጥለውት ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠው፤ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ በወንበዴዎች እጅ ወደቀ፤ ልብሱንም ገፍፈው ደበደቡት፤ በሞት አፋፍ ላይ ጥለውት ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ፤ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት፤ ደበደቡትም፤ በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ በመንገድ ላይ ሳለ ቀማኞች አግኝተውት ልብሱን ገፈፉት፤ ከደበደቡትም በኋላ ሊሞት ሲያጣጥር ጥለውት ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ። |
ስለዚህ እነሆ የተቀረጹትን ምስሎችዋን የምበቀልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርዋም ሁሉ የተገደሉት ይወድቃሉ።
ላሜድ። በከተማ ጎዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥ ነፍሳቸውም በእናቶቻቸው ብብት እለይ-እለይ ባለች ጊዜ፥ እናቶቻቸውን፥ “እህልና ወይን ወዴት አለ?” ይሉአቸዋል።
የባቢሎንንም ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም በእጁ እሰጣለሁ፤ ግብፅንም ይወጋበታል፥ ምርኮዋንም ይማርካል፤ ሰለባዋንም ይሰልባል።
ዐሥራ ሁለቱንም ወሰዳቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ በነቢያትም የተጻፈው ሁሉ በሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል።