ዘሌዋውያን 25:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኢዮቤልዩ ዓመት በኋላ እንደ ዓመታቱ ቍጥር ከባልንጀራህ ትገዛለህ፤ እርሱም እንደ መከሩ ዓመታት ቍጥር ይከፍልሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኢዮቤልዩ በኋላ ያሉትን ዓመታት ብዛት መሠረት በማድረግ ከወገንህ ትገዛለህ፤ እርሱም የቀሩትን የመከር ዓመታት ብዛት መሠረት በማድረግ ይሸጥልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኢዮቤልዩ በኋላ እንደ ዓመታቱ ቍጥር ከባልንጀራህ ትገዛለህ፤ እርሱም እንደ መከሩ ዓመታት ቍጥር ይሸጥልሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዋጋውም የሚተመነው ተከታዩ የንብረት መመለሻ ዓመት ከመግባቱ በፊት፥ ምድሪቱ ልታስገኝ በምትችለው ሰብል መጠን ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኢዮቤልዩ በኋላ እንደ ዓመታቱ ቍጥር ከባልንጀራህ ትገዛለህ፤ እርሱም እንደ መከሩ ዓመታት ቍጥር ይሸጥልሃል። |