ያ አምሳኛው ዓመት ለእናንተ ኢዮቤልዩ ይሆናል፤ በእርሱም አትዝሩ፤ የገቦውንም አትጨዱ፤ የተቀደሰውንም በእርሱ አትልቀሙ።
ዘሌዋውያን 25:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮቤልዩ ነውና የተቀደሰ ይሁንላችሁ፤ በሜዳ ላይ የበቀለውን ብሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮቤልዩ ስለ ሆነ ለእናንተ የተቀደሰ ይሁን፤ ሳትዘሩት በሜዳ የበቀለውን ብሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮቤልዩ ነውና የተቀደሰ ይሁንላችሁ፤ ምድሪቱ ራስዋ የምትሰጠውን ፍሬ ትበላላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓመቱ በሙሉ ለእናንተ የተቀደሰ ይሆናል፤ እርሻዎቻችሁ ማንም ሳይንከባከባቸው ራሳቸው የሚያስገኙትን ምግብ ብቻ ትበላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮቤልዩ ነውና የተቀደሰ ይሁንላችሁ፤ በሜዳ ላይ የበቀለውን ብሉ። |
ያ አምሳኛው ዓመት ለእናንተ ኢዮቤልዩ ይሆናል፤ በእርሱም አትዝሩ፤ የገቦውንም አትጨዱ፤ የተቀደሰውንም በእርሱ አትልቀሙ።