እንዲሁም ኀጢአት እንዳይሆንባቸው፥ እንዳይሞቱም፥ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገቡ፥ በመቅደሱም ያገለግሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናል፤ ለእርሱ፥ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።
ዘሌዋውያን 22:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡትን፥ በእስራኤል ልጆች ዘንድ የተቀደሰውን ነገር አያርክሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡትን የተቀደሰ መሥዋዕት ካህናቱ አያርክሱት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህናቱ የእስራኤል ልጆች ለጌታ የሚያቀርቡትን የተቀደሰውን ነገር አያርክሱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ለእግዚአብሔር የሚያመጡአቸውን የተቀደሱ ስጦታዎች፥ ካህናት ማርከስ የለባቸውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምቀድሳቸውም እግዚአብሔር እኔ ነኝና ከተቀደሰው በበሉ ጊዜ ኃጢአትንና በደልን እንዳይሸከሙ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡትን በእስራኤል ልጆች ዘንድ የተቀደሰውን ነገር አያርክሱ። |
እንዲሁም ኀጢአት እንዳይሆንባቸው፥ እንዳይሞቱም፥ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገቡ፥ በመቅደሱም ያገለግሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናል፤ ለእርሱ፥ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።
ካህናቷም ሕጌን ጣሱ፤ በመቅደሴም መካከል ቅድሳቴን አረከሱ፤ ከርኵሰትም አልራቁም፤ በንጹሕና በርኩስ መካከል ያለውንም ልዩነት አላወቁም፤ ዐይናቸውንም ከሰንበታቴ ሸፈኑ፤ እኔም በመካከላቸው ረከስሁ።
የበላውም ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን ነገር አርክሶአልና ኀጢአቱን ይሸከማል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።
በኀጢአት ሳሉ ከተቀደሰው መሥዋዕት ከበሉ ግን ኀጢአትና በደል ይሆንባቸዋል፤ የማነጻቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
ቢያረክሱአት እንዳይሞቱ፥ ስለ እርስዋም ኀጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ሕግን ይጠብቁ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝና።
የመጀመሪያውንም ከእርሱ ባነሣችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኀጢአት አይሆንባችሁም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤል ልጆች የቀደሱትን አታርክሱ።”