በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ይዛ ወደ ካህኑ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ታመጣቸዋለች።
ዘሌዋውያን 15:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም አንዲቱን ለኀጢአት መሥዋዕት፥ አንዲቱንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም ስለ ፈሳሽዋ ርኩስነት በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይላታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መሠረት ስለ ፈሳሿ ርኩሰት በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይላታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ስለ ፈሳሽዋም ርኩስነት ካህኑ በጌታ ፊት ያስተሰርይላታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም አንዱን ኃጢአት የሚሰረይበት መሥዋዕት፥ ሁለተኛውንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፤ በዚህም ዐይነት ካህኑ ስለሚፈሰው ርኲሰት በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይላታል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም ስለ ፈሳሽዋ ርኩስነት በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይላታል። |
በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ይዛ ወደ ካህኑ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ታመጣቸዋለች።
“ስለ ሠራው ኀጢአት የበግ መግዣ ገንዘብ በእጁ ባይኖረው ግን፥ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእግዚአብሔር ያቀርባል። ወደ ካህኑም ያመጣቸዋል፤