ዘሌዋውያን 15:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግዳጅም ሳለች የምትተኛበት ነገር ሁሉ ርኩስ ነው፤ የምትቀመጥበትም ነገር ሁሉ ርኩስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በወር አበባዋ ጊዜ የምትተኛበት ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል፤ የተቀመጠችበትም ነገር ርኩስ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በወር አበባዋ ጊዜ የምትተኛበት ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ የምትቀመጥበትም ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በወር አበባዋ ጊዜ የምትቀመጥበትም ሆነ የምትተኛበት ነገር ሁሉ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መርገምም ስትሆን የምትተኛበት ነገር ሁሉ ርኩስ ነው፤ የምትቀመጥበትም ነገር ሁሉ ርኩስ ነው። |
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረች ነገርን አገኘሁ፤ እርስዋም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ በእጆችዋም ማሰሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ደግ የሆነ ከእርሷ ያመልጣል። ኀጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
“ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት፥ በሥጋዋም ያለው ፈሳሽ ነገር ደም ቢሆን፥ በግዳጅዋ ሰባት ቀን ትቀመጣለች፤ የሚነካትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው።