ዳዊትም መልእክተኞችን ልኮ አስመጣት፤ ወደ እርሱም ገባች፤ ከርኵሰቷም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤቷም ተመለሰች።
ዘሌዋውያን 15:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴት ፈሳሽ ከአለበት ወንድ ጋር ብትገናኝ ሁለቱም በውኃ ይታጠባሉ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩሳን ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው ከአንዲት ሴት ጋራ ግብረ ሥጋ ፈጽሞ ዘር ቢፈስሰው፣ ሁለቱም በውሃ ይታጠቡ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩሳን ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንዱ ከሴቲቱ ጋር ተኝቶ ዘሩን ቢያፈስስ፥ ሁለቱ በውኃ ይታጠባሉ፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩሶች ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴትና ወንድ አብረው ተኝተው በሚነሡበት ጊዜ፥ ሁለቱም ሰውነታቸውን በውሃ ታጥበው እስከ ምሽት ድረስ የረከሱ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንዱ በሴቲቱ ቢደርስባት ሁለቱ በውኃ ይታጠባሉ፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩሶች ናቸው። |
ዳዊትም መልእክተኞችን ልኮ አስመጣት፤ ወደ እርሱም ገባች፤ ከርኵሰቷም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤቷም ተመለሰች።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፤ ከቤትህም ይነቅልሃል፥ ያፈልስሃልም፥ ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።
በሆነው ሁሉ ላይ ሥልጣን አለኝ፤ ግን ሁሉ የሚጠቅመኝ አይደለም፤ ሁሉም ይቻለኛል፤ ነገር ግን በእኔ ላይ እንዲሠለጥን የማደርገው ምንም የለም።
ከዝሙት ራቁ፤ ኀጢአት የሚሠራ ሰው ሁሉ ከሥጋው ውጭ ይሠራልና፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን ራሱ በሥጋው ላይ ኀጢአትን ይሠራል።
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመኝታቸውም ርኵሰት የለውም፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።