ይህችን በልቤ አኖራለሁ፤ ስለዚህ እታገሣለሁ።
ሆኖም ይህን ዐስባለሁ፤ እንግዲያስ ተስፋ አለኝ፤
ይህችን በልቤ አኖራለሁ፥ ስለዚህ እታገሣለሁ።
ሆኖም ይህን አንድ ነገር በማስብበት ጊዜ በተስፋ እሞላለሁ።
ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና።
ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይቸኵላል፥ እርሱም አይዋሽም፣ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፣ እርሱ አይዘገይም።