መሳፍንት 9:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሜሌክም ከእርሱም ጋር ያሉት ሠራዊት በከተማዪቱ መግቢያ በር ሸምቀው ቆሙ። እነዚያ ሁለቱ ሠራዊት ግን ወደ ጫካው ተበትነው አጠፉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አቢሜሌክና ዐብረውት የነበሩ ምድቦች ቦታ ለመያዝ በፍጥነት ወደ ከተማዪቱ መግቢያ በሚሮጡበት ጊዜ፣ ሌሎቹ ሁለት ምድቦች ደግሞ እየሮጡ ሄደው በዕርሻው ያሉትን ሁሉ ፈጇቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አቤሜሌክና አብረውት የነበሩ ምድቦች ቦታ ለመያዝ በፍጥነት ወደ ከተማይቱ መግቢያ በሚሮጡበት ጊዜ፥ ሌሎቹ ሁለት ምድቦች ደግሞ እየሮጡ ሄደው በዕርሻው ያሉትን ሁሉ ፈጇቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር የተመደበው ቡድን የከተማይቱን ቅጽር በር ለመጠበቅ ተጣድፈው ወጥተው በከተማው መግቢያ በር ላይ ቆሙ፤ የቀሩት ሁለቱ ቡድኖች በመስኩ በተገኙት ላይ አደጋ ጥለው ፈጁአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሜሌክም ከእርሱም ጋር ያሉት ወገኖች ተጣደፉ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሙ፥ ሁለቱም ወገኖች በእርሻው ውስጥ በነበሩት ሁሉ ላይ ሮጡባቸው፥ መቱአቸውም። |
ዶግም ዛፎቹን፦ በእውነት እኔን በእናንተ ላይ ካነገሣችሁኝ እሳት ከዶግ ወጥቶ የሊባኖስን ዝግባ ካልበላው ከጥላዬ በታች ታርፉ ዘንድ ኑ አለቻቸው።
እንዲህ ባይሆን ግን ከአቤሜሌክ እሳት ትውጣ፤ የሰቂማንም ሰዎች፥ የመሐሎንንም ቤት ትብላ፤ ያም ባይሆን ከሰቂማ ሰዎች ከመሐሎንም ቤት እሳት ትውጣ፤ አቤሜሌክንም ትብላው።”
ሕዝቡንም ወስዶ በሦስት ወገን ከፈላቸው፤ በሜዳም ሸመቀ፤ ተመለከተም፤ እነሆም፥ ሕዝቡ ከከተማ ወጡ፤ ተነሣባቸውም፤ ገደላቸውም።
አቤሜሌክም በዚያ ቀን ሁሉ ከከተማዪቱ ጋር ተዋጋ፤ ከተማዪቱንም ይዞ በእርስዋ የነበሩትን ሕዝብ ገደለ፤ ከተማዪቱንም አፈረሰ፤ ጨውም ዘራባት።