መሳፍንት 9:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም አንተና ከአንተ ጋር ያሉት ሕዝብ በሌሊት ተነሡ፤ በሜዳም ሸምቁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በሌሊት ሰዎችህን ይዘህ ወጥተህ ሜዳው ላይ ማድፈጥ አለብህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በሌሊት ሰዎችህን ይዘህ ወጥተህ ሜዳው ላይ ማድፈጥ አለብህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ አንተና ተከታዮችህ በሌሊት ከዚያ ተነሥታችሁ በመስክ ውስጥ ደፈጣ አድርጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም አንተና ከአንተ ጋር ያሉት ሕዝብ በሌሊት ተነሡ፥ በሜዳም ሸምቁ፥ ነገም ፀሐይ በወጣች ጊዜ ማልደህ ተነሣ፥ በከተማይቱም ላይ ውደቅባት፥ እነሆም፥ እርሱና ከእርሱ ጋር ያሉት ሕዝብ በአንተ ላይ በወጡ ጊዜ እጅህ እንዳገኘች አድርግበት። |
ኢያሱም፥ ተዋጊዎቹም ሕዝብ ሁሉ ተነሥተው ወደ ጋይ ወጡ፤ ኢያሱም ጽኑዓን፥ ተዋጊዎችና ኀያላን የሆኑትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መረጠ፤ በሌሊትም ላካቸው።
እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “እነሆ፥ ሂዱና ከከተማዪቱ በስተኋላ ተደበቁ፤ ከከተማዪቱ አትራቁ፤ ሁላችሁም ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ፤
እንዲህም ብሎ ወደ አቤሜሌክ ከእጅ መንሻ ጋር መልእክተኞችን ላከ፥ “እነሆ፥ የአቤድ ልጅ ገዓልና ወንድሞቹ ወደ ሰቂማ መጥተዋል፤ እነሆም፥ በአንተ ምክንያት ከተማዪቱን ይወጓታል።
ነገም ፀሐይ በወጣች ጊዜ ማልደህ ተነሣ፤ ከተማዪቱንም ክበባት፤ እነሆም፥ እርሱና ከእርሱ ጋር ያሉት ሕዝብ በአንተ ላይ በወጡ ጊዜ እጅህ እንዳገኘች አድርግበት።”