ጌዴዎንም ሕልሙንና ትርጓሜዉን በሰማ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ ወደ እስራኤልም ሰፈር ተመልሶ፥ “እግዚአብሔር የምድያምን ሠራዊት በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተነሡ” አለ።
መሳፍንት 8:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌዴዎንም፥ “እግዚአብሔር ዛብሄልንና ስልማናን በእጄ አሳልፎ ቢሰጠኝ እኔ በምድረ በዳ እሾህና በኩርንችት ሥጋችሁን እገርፋለሁ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌዴዎንም መልሶ፣ “ደኅና፤ እግዚአብሔር ዛብሄልንና ስልማናን በእጄ አሳልፎ በሚሰጥበት ጊዜ በምድረ በዳ እሾኽና አሜከላ ሥጋችሁን እተለትላለሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌዴዎንም መልሶ፥ “እንግዲህ ደህና፤ ጌታ ዜባሕንና ጻልሙናን በእጄ አሳልፎ በሚሰጥበት ጊዜ በምድረ በዳ እሾኽና አሜከላ ሥጋችሁን እገርፋለሁ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌዴዎንም “ደግ ነው! እግዚአብሔር በዜባሕና በጻልሙናዕ ላይ ድልን በሚያጐናጽፈኝ ጊዜ ከበረሓ በሚገኙ እሾኽና አሜከላ እገርፋችኋለሁ!” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌዴዎንም፦ እግዚአብሔር ዛብሄልንና ስልማናን በእጄ አሳልፎ ሲሰጠኝ እኔ በምድረ በዳ እሾህና በኩርንችት ሥጋችሁን እገርፋለሁ አለ። |
ጌዴዎንም ሕልሙንና ትርጓሜዉን በሰማ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ ወደ እስራኤልም ሰፈር ተመልሶ፥ “እግዚአብሔር የምድያምን ሠራዊት በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተነሡ” አለ።
የሱኮትንም ሰዎች፥ “ተርበዋልና እኔን ለተከተሉ ሰዎች እባካችሁ እህል ስጡአቸው፤ እኔም የምድያምን ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን አሳድዳለሁ” አላቸው።