መሳፍንት 8:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢዮአስም ልጅ ጌዴዎን በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ በአብያዜራውያንም ከተማ በኤፍራታ በነበረችው በአባቱ በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ በአቢዔዝራውያን ምድር ባለችው በዖፍራ፣ በአባቱ በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ በአቢዔዝራውያን ምድር ባለችው በዖፍራ፥ በአባቱ በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ በአባቱም በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ፤ ይህም መቃብር የአቢዔዜር ጐሣ ከተማ በነበረችው በዖፍራ ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢዮአስም ልጅ ጌዴዎን በመልካም ሽምግልና ሞተ፥ በአቢዔዝራውያንም ከተማ በዖፍራ በነበረችው በአባቱ በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ። |
አሣሄልንም አንሥተው በቤተ ልሔም በአባቱ መቃብር ቀበሩት፤ ኢዮአብና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ፤ ሄዱ፥ በኬብሮንም አነጉ።
በወራቱ የደረሰ አዝመራ እንዲሰበሰብ፥ የእህሉ ነዶም በወቅቱ ወደ አውድማ እንዲገባ፥ በረዥም ዕድሜ ወደ መቃብር ትገባለህ።
ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም እስከ ዛሬ ድረስ “የእግዚአብሔር ሰላም” ብሎ ጠራው። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ ለኤዝሪ አባት በሆነችው በኤፍራታ አለ።
ጌዴዎንም ምስል አድርጎ ሠራው፤ በከተማውም በኤፍራታ አኖረው፤ እስራኤልም ሁሉ ተከትሎ አመነዘረበት፤ ለጌዴዎንና ለቤቱም ወጥመድ ሆነ።
እንዲህም ሆነ፤ ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመለሱ፤ በዓሊምንም ተከትለው አመነዘሩ፤ በዓሊምም አምላክ ይሆናቸው ዘንድ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገቡ።