ዛብሄልና ስልማናም ሸሹ፤ እርሱም አሳደዳቸው፤ ሁለቱንም የምድያም ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን ያዘ፤ ጌዴዎንም ሠራዊቱን ሁሉ አጠፋ።
መሳፍንት 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎንም ከአሬስ ዳገት ከጦርነት ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን በሐሬስ መተላለፊያ በኩል አድርጎ ከጦርነቱ ተመለሰ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን በሐሬስ ዳገት በኩል ከጦርነቱ ተመለሰ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን በሔሬስ ዳገት በኩል ከጦርነት ተመለሰ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢዮአስ ልጅም ጌዴዎን ከሔሬስ ዳገት ከሰልፍ ተመለሰ። |
ዛብሄልና ስልማናም ሸሹ፤ እርሱም አሳደዳቸው፤ ሁለቱንም የምድያም ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን ያዘ፤ ጌዴዎንም ሠራዊቱን ሁሉ አጠፋ።
ከሱኮትም ሰዎች አንድ ብላቴና ይዞ መረመረው፤ እርሱም ሰባ ሰባቱን የሱኮትን አለቆችና ሽማግሌዎችን አስቈጠራቸው።