መሳፍንት 8:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛብሄልና ስልማናም ሸሹ፤ እርሱም አሳደዳቸው፤ ሁለቱንም የምድያም ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን ያዘ፤ ጌዴዎንም ሠራዊቱን ሁሉ አጠፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለቱ የምድያም ነገሥታት ዛብሄልና ስልማና ሸሹ፤ ጌዴዎን ግን አሳድዶ ያዛቸው፤ መላ ሰራዊታቸውንም እጅግ በታተነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱ የምድያም ነገሥታት ዛብሄልና ጻልሙና ሸሹ፤ ጌዴዎን ግን አሳዶ ያዛቸው፤ መላ ሠራዊታቸውንም እጅግ በታተነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱ የምድያማውያን ነገሥታት ዜባሕና ጻልሙናዕ ሸሹ፤ ነገር ግን ጌዴዎን አሳዶ ማረካቸው፤ ሠራዊታቸውንም በሙሉ በድንጋጤ ላይ እንዲወድቁ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛብሄልና ስልማናም ሸሹ፥ እርሱም አሳደዳቸው፥ ሁለቱንም የምድያም ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን ያዘ፥ ሠራዊቱንም ሁሉ አስደነገጠ። |
እግዚአብሔር አምላክ ምጽዋትንና እውነትን ይወድዳልና፥ እግዚአብሔር ክብርና ሞገስን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከበረከቱ አያሳጣቸውም።
ጌዴዎንም በድንኳን የሚኖሩ ሰዎች ባሉበት መንገድ በኖቤትና በዮግቤል በምሥራቅ በኩል ወጣ፤ ሠራዊቱም ተዘልሎ ሳለ አጠፋቸው።