የአቤሴሎምም አገልጋዮች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥተው፥ “አኪማሆስና ዮናታን የት አሉ?” አሉ፤ ሴቲቱም፥ “ፈፋውን ተሻግረው ሄዱ፤ ጥቂትም ቀደሙአችሁ” አለቻቸው። እነርሱም ፈልገው አጡአቸው፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሱ።
መሳፍንት 4:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ከድንኳኑ ደጃፍ ቁሚ፤ ሰውም መጥቶ፦ ‘በዚህ ሰው አለን?’ ብሎ ቢጠይቅሽ አንቺ፦ ‘የለም’ ትዪዋለሽ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “በድንኳኑ በር ላይ ቁሚ፤ ማንም ሰው መጥቶ፣ ‘እዚህ ሰው አለ?’ ቢልሽ፣ ‘የለም’ በይ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፥ “በድንኳኑ በር ላይ ቁሚ፤ ማንም ሰው መጥቶ፥ ‘እዚህ ሰው አለ?’ ቢልሽ፥ ‘የለም በይ’” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እርሱ “በድንኳኑ በር ላይ ቁሚ፤ አንድ ሰው መጥቶ ከዚህ ሌላ ሰው እንዳለ ቢጠይቅሽ ማንም የለም በይው” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ከድንኳኑ ደጃፍ ቁሚ፥ ሰውም መጥቶ፦ በዚህ ሰው አለን? ብሎ ቢጠይቅሽ አንቺ፦ የለም ትዪዋለሽ አላት። |
የአቤሴሎምም አገልጋዮች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥተው፥ “አኪማሆስና ዮናታን የት አሉ?” አሉ፤ ሴቲቱም፥ “ፈፋውን ተሻግረው ሄዱ፤ ጥቂትም ቀደሙአችሁ” አለቻቸው። እነርሱም ፈልገው አጡአቸው፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሱ።
ሲሣራም፥ “ጠምቶኛልና እባክሽ የምጠጣው ጥቂት ውኃ ስጪኝ” አላት፤ እርስዋም የወተቱን ዕቃ ፈትታ አጠጣችው፤ ፊቱንም ሸፈነችው።
የሔቤርም ሚስት ኢያዔል የድንኳኑን ካስማ ወሰደች፤ በሁለተኛ እጅዋም መዶሻ ያዘች፤ ቀስ ብላም ወደ እርሱ ቀረበች፤ በጆሮ ግንዱም ካስማውን ቸነከረችበት፤ እርሱም ደክሞ አንቀላፍቶ ነበርና ካስማው ወደ መሬት ጠለቀ፤ እርሱም ከእግርዋ በታች ተንፈራፈረ፤ ተዘርሮም ሞተ።