መሳፍንት 4:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባርቅም ሰረገሎችንና ሠራዊቱን እስከ አሕዛብ አሪሶት ድረስ አባረረ፤ የሲሣራም ሠራዊት ሁሉ በሰይፍ ስለት ወደቀ፤ አንድ እንኳ አልቀረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባርቅ ግን የሲሣራን ሠረገሎችና ሰራዊቱን እስከ አሪሶት ሐጎይም ድረስ አሳደዳቸው፤ የሲሣራ ሰራዊት በሙሉ በሰይፍ ወደቀ፤ በሕይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባራቅ ግን የሲሣራን ሠረገሎችና ሠራዊቱን እስከ ሐሮሼት ሐጎይም ድረስ አሳደዳቸው፤ የሲሣራ ሠራዊት በሙሉ በሰይፍ ወደቀ፤ በሕይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባራቅም ሠረገሎቹንና ሠራዊቱን የአሕዛብ ይዞታ እስከ ሆነችው እስከ ሐሮሼት ድረስ አሳደዳቸው፤ የሲሣራም ሠራዊት በሙሉ በሰይፍ ተገደሉ፤ አንድ ሰው እንኳ አልተረፈም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባርቅም ሰረገሎችንና ሠራዊቱን እስከ አሪሶት ድረስ አባረረ፥ የሲሣራም ሠራዊት ሁሉ በሰይፍ ስለት ወደቀ፥ አንድ እንኳ አልቀረም። |
ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ።
ውኃውም ተመልሶ በኋላቸው ወደ ባሕር የገቡትን ሰረገሎችን፥ ፈረሰኞችንም፥ የፈርዖንንም ሠራዊት ሁሉ ከደነ፤ ከመጡትም ሁሉ አንድ ስንኳ የቀረ የለም።
እግዚአብሔር ሰረገላውንና ፈረሱን ሠራዊቱንና አርበኛውን ያወጣል፤ እነርሱ ግን በአንድነት ተኝተዋል፤ አይነሡም፤ ቀርተዋል፤ እንደ ጥዋፍ ኩስታሪም ጠፍተዋል፤
እግዚአብሔርም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ መቱአቸውም፤ ወደ ታላቂቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴሮንም፥ በምሥራቅም በኩል ወዳለው ወደ ሞሳሕ ሸለቆ አሳደዱአቸው፤ ማንንም ሳያስቀሩ መቱአቸው።
ሲሣራም ወደ ጓደኛው ወደ ቄናዊው ወደ ሔቤር ሚስት ወደ ኢያዔል ድንኳን በእግሩ ሸሸ፤ በአሶር ንጉሥ በኢያቢንና በቄናዊው በሔቤር ቤት መካከል ሰላም ነበርና።
እግዚአብሔርም በአሦር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቢን እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ የሠራዊቱም አለቃ ሲሣራ ነበረ፤ እርሱም በአሕዛብ አሪሶት ይቀመጥ ነበረ።