ማኅበሩም ወደዚያ ዐሥራ ሁለት ሺህ ኀያላን ሰዎችን ልከው፥ “ሂዱ በኢያቢስ ገለዓድም ያሉትን ሰዎች ሴቶችንም ሕዝቡንም በሰይፍ ስለት ግደሉ።
መሳፍንት 21:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም በተቈጠሩ ጊዜ፥ እነሆ፥ ከኢያቢስ ገለዓድ ነዋሪዎች ሰው አልተገኘም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡን ሲቈጥሩም ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች አንድም ሰው አልነበረምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡን ሲቈጥሩም ከያቤሽ ገለዓድ ሰዎች አንድም ሰው አልነበረምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሠራዊቱን ለመቊጠር በያንዳንዱ ስም በሚጠራበት ጊዜ ከያቤሽ ወገን አንድም ሰው አልነበረም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም በተቈጠሩ ጊዜ፥ እነሆ፥ በኢያቢስ ገለዓድ የሚኖር ሰው አልተገኘም። |
ማኅበሩም ወደዚያ ዐሥራ ሁለት ሺህ ኀያላን ሰዎችን ልከው፥ “ሂዱ በኢያቢስ ገለዓድም ያሉትን ሰዎች ሴቶችንም ሕዝቡንም በሰይፍ ስለት ግደሉ።
እነርሱም፥ “ከእስራኤል ነገድ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ ያልወጣ ማን ነው?” አሉ። እነሆም፥ ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባኤው ማንም አልወጣም ነበር።
የእግዚአብሔር መልአክ አለ፥ “ሜሮዝን ርገሙ፤ ወደ እግዚአብሔር ርዳታ አልመጡምና፥ በኀያላን መካከል ወደ እርሱ ርዳታ አልመጡምና፥ በቤቶችዋ ያሉትን ሰዎች ፈጽማችሁ ርገሙ።”