መሳፍንት 20:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ ሁላችሁ፥ ምክራችሁንና እዝናታችሁን በዚህ ስጡ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም እናንተ እስራኤላውያን ሁሉ በጕዳዩ ላይ ተወያዩበት፤ ፍርዳችሁንም ስጡ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም እናንተ እስራኤላውያን ሁሉ በጉዳዩ ላይ ተወያዩበት፤ ፍርዳችሁንም ስጡ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚህ ያላችሁት እስራኤላውያን ሁሉ ምክራችሁንና ፍርዳችሁን ስጡ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ ሁላችሁ፥ ምክራችሁንና እዝናታችሁን በዚህ ስጡ። |
በእናንተ ላይ ዝሙት ይሰማል፤ እንደዚህ ያለው ዝሙትም አረማውያን እንኳ የማያደርጉት ነው፤ ያባቱን ሚስት ያገባ አለና።
ጠብቁት፤ አድርጉትም፤ ይህን ሥርዐት ሁሉ ሰምተው፦ እነሆ፥ ‘ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው’ በሚሉ በአሕዛብ ፊት ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ይህ ነውና፤
ከዚያም በኋላ ያያት ሁሉ እንዲህ አለ፥ “እስራኤል ከግብፅ ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር የሆነበት ጊዜ የለም፤ የታየበትም ጊዜ የለም፤” ያም ሰው እነዚያን የላካቸውን ሰዎች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፥ “የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በሏቸው፦ እስራኤል ከግብፅ ከወጡ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ እንዲህ የሆነበት ጊዜ አለን? እናንተ ተመካከሩበት፤ የሚበጀውንም ተነጋገሩ።”