አሞሬዎናውያንም የዳንን ልጆች በተራራማው ሀገር አስጨነቁአቸው፤ ወደ ሸለቆው እንዲወርዱ አይፈቅዱላቸውም ነበርና።
መሳፍንት 18:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም። እስከዚያም ቀን ድረስ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልደረሳቸውም ነበርና በዚያ ዘመን የዳን ነገድ የሚቀመጡባት ርስት ይሹ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም። የዳን ነገድም በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስተ ድርሻውን ገና ስላልወሰደ፣ የሚሰፍርበትን የራሱን ርስት ይፈልግ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ የዳን ነገድም በእስራኤል ነገዶች መካከል የርስት ድርሻውን ገና ስላልወሰደ፥ የሚሰፍርበትን የራሱን ርስት ይፈልግ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ በእስራኤል ነገዶች መካከል የራሳቸው የሆነ የርስት ድርሻ ገና ያላገኙ ስለ ነበሩ የዳን ነገድ ተወላጆች የሚሰፍሩበትን ርስት ለማግኘት በመፈለግ ላይ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም። እስከዚያም ቀን ድረስ ለዳን ነገድ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልደረሳቸውም ነበርና በዚያ ዘመን የሚቀመጡባት ርስት ይሹ ነበር። |
አሞሬዎናውያንም የዳንን ልጆች በተራራማው ሀገር አስጨነቁአቸው፤ ወደ ሸለቆው እንዲወርዱ አይፈቅዱላቸውም ነበርና።
በዚያም ዘመን ለእስራኤል ንጉሥ አልነበራቸውም። በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር ማዶ የተቀመጠ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፤ ከይሁዳ ቤተ ልሔምም ዕቅብት አገባ።