Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 21:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በዚ​ያም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ ሰው ሁሉ በፊቱ መል​ካም መስሎ የታ​የ​ውን ያደ​ርግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱም ሰው መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱም ሰው መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በዚያም ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱም ሰው ለራሱ ደስ ያለውን ነገር ሁሉ እንደ ፈለገ ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፥ ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 21:25
13 Referencias Cruzadas  

የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ኝም እኔ ብና​ወጥ ደስ እን​ዳ​ይ​ላ​ቸው፥


በሰዎች ዘንድ ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን ወደ ሲኦል ጕድጓድ ታደርሳለች።


በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታምነህ ኑር፥ በራስህም ጥበብ አትደገፍ፤


አንተ ጐበዝ፥ በጕ​ብ​ዝ​ናህ ደስ ይበ​ልህ፥ በጕ​ብ​ዝ​ና​ህም ወራት ልብ​ህን ደስ ይበ​ለው፥ በል​ብ​ህም መን​ገድ፥ ዐይ​ኖ​ች​ህም በሚ​ያ​ዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለ​ዚህ ነገር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ፍርድ እን​ዲ​ያ​መ​ጣህ ዕወቅ።


እኛ ሁላ​ችን እንደ በጎች ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ገዛ መን​ገዱ አዘ​ነ​በለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጠው።


በሬን የሚ​ሠ​ዋ​ልኝ ኃጥእ ውሻን እን​ደ​ሚ​ያ​ር​ድ​ልኝ ነው፤ የእ​ህ​ልን ቍር​ባን የሚ​ያ​ቀ​ር​ብም የእ​ሪ​ያን ደም እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ርብ ነው፤ ዕጣ​ን​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢያ የሚ​ያ​ጥን አም​ላ​ክን እን​ደ​ሚ​ፀ​ርፍ ነው፤ እነ​ዚህ የገዛ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን መረጡ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ይላ​ታል።


ሰው ሁሉ በፊቱ መል​ካም መስሎ የታ​የ​ውን፥ እኛ በዚህ ዛሬ የም​ና​ደ​ር​ገ​ውን ሁሉ አታ​ድ​ርጉ፤


በዚ​ያም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ ሰውም ሁሉ በፊቱ መል​ካም መስሎ የታ​የ​ውን ያደ​ርግ ነበር።


በዚ​ያም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም። እስ​ከ​ዚ​ያም ቀን ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች መካ​ከል ርስት አል​ደ​ረ​ሳ​ቸ​ውም ነበ​ርና በዚያ ዘመን የዳን ነገድ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ርስት ይሹ ነበር።


አም​ስ​ቱም ሰዎች ሄዱ፤ ወደ ሌሳም ደረሱ፤ በው​ስ​ጡም የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ተዘ​ል​ለው አዩ​አ​ቸው፤ እንደ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም ልማድ ጸጥ ብለው፥ ዐር​ፈው፥ ተዘ​ል​ለ​ውም ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ በተ​መ​ዘ​ገ​በች የር​ስ​ታ​ቸው ምድ​ርም ቃልን መና​ገር አል​ቻ​ሉም፤ ከሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ንም ርቀው ይኖሩ ነበር። ከሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም ጋር ግን​ኙ​ነት አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም።


በዚ​ያም ዘመን ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም። በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ማዶ የተ​ቀ​መጠ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፤ ከይ​ሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ዕቅ​ብት አገባ።


በዚያ ጊዜም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከዚያ ተነሡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ወገ​ኑና ወደ ነገዱ ሄደ፤ ሰውም ሁሉ ከዚያ ወደ ርስቱ ተመ​ለሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos