መሳፍንት 14:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ የፍየል ጠቦትን እንደሚጥልም ጣለው፤ በእጁም እንደ ኢምንት ሆነ፤ ያደረገውንም ለአባቱና ለእናቱ አልተናገረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በኀይል ወረደበት፤ ስለዚህ የፍየል ጠቦት እንደሚገነጣጠል አንበሳውን ያለ ምንም መሣሪያ በባዶ እጁ ገነጣጠለው፤ ያደረገውን ግን ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ የጌታ መንፈስ በኃይል ወረደበት፤ ስለዚህ የፍየል ጠቦት እንደሚገነጣጠል አንበሳውን ያለ ምንም መሣሪያ በባዶ እጁ ገነጣጠለው፤ ያደርገውን ግን ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድንገትም የእግዚአብሔር መንፈስ ሶምሶንን አበረታው፤ ስለዚህም አንበሳውን እንደ አንድ የፍየል ጠቦት ያኽል በመቊጠር ያለ ምንም መሣሪያ በባዶ እጁ ገነጣጥሎ ጣለው፤ ያደረገውንም ነገር ለወላጆቹ አልነገራቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል ወረደ፥ ጠቦትን እንደሚቆራርጥ በእጁ ምንም ሳይኖር ቈራረጠው፥ ያደረገውንም ለአባቱና ለእናቱ አልነገረም። |
መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እነርሱ በእምነት ተጋደሉ፤ ነገሥታትን ድል ነሡ፤ ጽድቅን አደረጉ፤ ተስፋቸውን አገኙ፤ የአናብስትንም አፍ ዘጉ ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፤ እርሱም የምናሴ ዕጣ ከምትሆን ከገለዓድ ምድርና ከገለዓድ መሴፋ፥ ወደ አሞን ልጆች ማዶ ተሻገረ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስቀሎናም ወረደ፤ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፤ ልብሳቸውንም ገፍፎ እንቆቅልሹን ለነገሩት ሰዎች ሰጠ። ሶምሶንም ተቈጣ፤ ወደ አባቱም ቤት ተመለሰ።
ሶምሶንም፥ አባቱና እናቱም ወደ ቴምናታ ወረዱ፤ በቴምናታም ወዳለው ወደ ወይኑ ስፍራ ፈቀቅ አለ፤ እነሆም፥ የአንበሳ ደቦል እያገሣ መጣበት።
ሶምሶንም፥ “ከፍልስጥኤማውያን ጋር ነፍሴ ትውጣ” አለ፤ ተጎንብሶም ምሰሶዎቹን በሙሉ ኀይሉ ገፋቸው፤ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመሳፍንቱ፥ በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፤ በሞቱም የገደላቸው ሙታን በሕይወቱ ሳለ ከገደላቸው በዙ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፤ ለጦርነትም ወጣ፤ እግዚአብሔርም በወንዞች መካከል ያለች የሶርያ ንጉሥ ኩሳርሳቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩሳርሳቴም ላይ በረታች።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በአንተ ይወርዳል፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፤ እንደ ሌላም ሰው ሆነህ ትለወጣለህ።
በነጋም ጊዜ፥ የሳኦል ልጅ ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፤ በዚያ በኩል ወዳለው ወደ ፍልስጥኤማውያን ሰፈር እንለፍ” አለው፤ ለአባቱም አልነገረውም።
እግዚአብሔር ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እመታህማለሁ፤ ራስህንም ከአንተ እቈርጠዋለሁ፤ ሬሳህንና የፍልስጥኤማውያንንም ሠራዊት ሬሶች ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ዛሬ እሰጣለሁ። ምድር ሁሉ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር እንዳለ ያውቃሉ፤