ሴቲቱም ወደ ባልዋ መጥታ፥ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፤ ከወዴትም እንደ መጣ ጠየቅሁት፥ እርሱም ስሙን አልነገረኝም።
መሳፍንት 13:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች ለባልዋም፥ “እነሆ፥ አስቀድሞ ወደ እኔ የመጣው ያ ሰው ደግሞ ተገለጠልኝ” ብላ ነገረችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ለባሏ ለመንገር ፈጥና በመሄድ፣ “ባለፈው ጊዜ የተገለጠልኝ ሰው ዛሬም ተገለጠልኝ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ለባሏ ለመንገር ፈጥና በመሄድ፥ “ባለፈው ጊዜ የተገለጠልኝ ሰው ዛሬም ተገለጠልኝ” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በፍጥነት ወደ እርሱ ሮጣ በመሄድ “እነሆ! ያ ከዚህ በፊት ወደ እኔ መጥቶ የነበረው ሰው ዛሬም እንደገና ተገለጠልኝ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች ለባልዋም፦ እነሆ፥ በቀደም ዕለት ወደ እኔ የመጣው ሰው ደግሞ ተገለጠልኝ ብላ ነገረችው። |
ሴቲቱም ወደ ባልዋ መጥታ፥ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፤ ከወዴትም እንደ መጣ ጠየቅሁት፥ እርሱም ስሙን አልነገረኝም።
እግዚአብሔርም የማኑሄን ቃል ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ እንደ ገና በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች ወደ ሴቲቱ መጣ፤ ባልዋ ማኑሄ ግን ከእርስዋ ጋር አልነበረም።