የአሞንም ልጆች የዳዊት ወገኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከቤትሮዖብ ሶርያውያንና ከሱባ ሶርያውያን ሃያ ሺህ እግረኞችን፥ ከአማሌቅ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎችን፥ ከአስጦብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ።
መሳፍንት 11:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የገለዓድ ሽማግሌዎችም ዮፍታሔን ከጦብ ምድር ለማምጣት ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የገለዓድ አለቆች ዮፍታሔን ለማምጣት ወደ ጦብ ምድር ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የገለዓድ አለቆች ዮፍታሔን ለማምጣት ወደ ጦብ ምድር ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም በሆነ ጊዜ የገለዓድ መሪዎች ዮፍታሔን ከጦብ ምድር መልሰው ለማምጣት ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሞንም ልጆች ከእስራኤል ጋር በተዋጉ ጊዜ የገለዓድ ሽማግሌዎች ዮፍታሔን ከጦብ ምድር ለማምጣት ሄዱ። |
የአሞንም ልጆች የዳዊት ወገኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከቤትሮዖብ ሶርያውያንና ከሱባ ሶርያውያን ሃያ ሺህ እግረኞችን፥ ከአማሌቅ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎችን፥ ከአስጦብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ።
የአሞንም ልጆች ወጥተው በበሩ መግቢያ ፊት ለፊት ይዋጉ ጀመሩ፤ የሱባና የሮዖብ ሶርያውያን፥ የአስጦብና የአማሌቅም ሰዎች ለብቻቸው በሰፊ ሜዳ ላይ ነበሩ።
የአሞንም ልጆች ከይሁዳ፥ ከብንያምና ከኤፍሬም ቤት ጋር ደግሞ ሊዋጉ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ እስራኤልም እጅግ ተጨነቁ።
ሕዝቡም ሳሙኤልን፥ “ሳኦል አይንገሥብን ያሉ እነማን ናቸው? እነዚያን ሰዎች አውጡአቸውና እንግደላቸው” አሉት።