“መንግሥታትንና አሕዛብን ዕድል ፈንታ አድርገህ ሰጠሃቸው፤ የሐሴቦንን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ።
መሳፍንት 11:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴዎንም እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ሴዎን ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፤ በኢያሴርም ሰፈረ፤ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴዎን ግን በግዛቱ እንዲያልፍ ለመፍቀድ እስራኤልን አላመነውም፤ ሰራዊቱንም ሰብስቦ በያሀጽ ከሰፈረ በኋላ ከእስራኤል ጋራ ተዋጋ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴዎን ግን በግዛቱ እንዲያልፍ ለመፍቀድ እስራኤልን አላመነውም፤ ሠራዊቱንም ሰብስቦ በያሃጽ ከሰፈረ በኋላ ከእስራኤል ጋር ተዋጋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሲሖን ግን እስራኤላውያን አልፈው እንዲሄዱ አልፈቀደላቸውም፤ እንዲያውም መላ ሠራዊቱን ሰብስቦ በያሐጽ በመስፈር ከእስራኤል ጋር ተዋጋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴዎንም እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ አላመነውም ነበር፥ ነገር ግን ሴዎን ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ በያሀጽም ሰፈረ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ። |
“መንግሥታትንና አሕዛብን ዕድል ፈንታ አድርገህ ሰጠሃቸው፤ የሐሴቦንን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ።
እስራኤልም ወደ አሞራዊው ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልእክተኞችን ላከ፤ እስራኤልም፦ ‘በምድርህ በኩል ወደ ስፍራችን፥ እባክህ፥ አሳልፈን’ አለው።
የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር ሴዎንንና ሕዝቡን ሁሉ በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠ፤ ገደሉአቸውም፤ እስራኤልም በዚያ ምድር ተቀምጠው የነበሩትን የአሞሬዎናውያንን ምድር ሁሉ ወረሱ።