ዓስካም፥ “በረከትን ስጠኝ፤ ወደ ደቡብ በረሃ ሰድደኸኛልና ውኃ የማጣቴን ዋጋ ደግሞ ስጠኝ” አለችው። ካሌብም በልብዋ እንደ ተመኘችው የመከራዋንና የኀዘኗን ዋጋ ሰጣት።
መሳፍንት 1:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ የእርሻ ቦታ ይሰጣት ዘንድ አባቷን እንድትለምነው ጎቶንያል መከራት። እርስዋም በአህያዋ ላይ ሆና አንጐራጐረች፤ “ወደ ደቡብ ሰድደኸኛል” ብላም ጮኸች። ካሌብም፥ “ምን ሆነሻል?” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ወደ ጎቶንያል በመጣች ጊዜ፣ አባቷ የዕርሻ መሬት እንዲሰጠው ይለምነው ዘንድ አጥብቃ ነገረችው፤ ካሌብም እርሷ ከአህያዋ ላይ እንደ ወረደች “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ወደ ዖትኒኤል በመጣች ጊዜ፥ ከአባቷ የእርሻ መሬት እንዲጠይቅ መከረችው፤ ካሌብም እርሷ ከአህያዋ ላይ እንደወረደች “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጋብቻቸውም ቀን ዖትኒኤል ዓክሳን “አባትሽ የእርሻ መሬት እንዲሰጥሽ ጠይቂ” አላት፤ እርስዋም ካሌብን ስታይ ከበቅሎዋ ላይ ወረደች፤ ካሌብም “ምን እንድሰጥሽ ትፈልጊአለሽ” ብሎ ጠየቃት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ እንዲለምን መከረችው። እርስዋም ከአህያዋ ወረደች፥ ካሌብም፦ ምን ፈለግሽ? አላት። |
ዓስካም፥ “በረከትን ስጠኝ፤ ወደ ደቡብ በረሃ ሰድደኸኛልና ውኃ የማጣቴን ዋጋ ደግሞ ስጠኝ” አለችው። ካሌብም በልብዋ እንደ ተመኘችው የመከራዋንና የኀዘኗን ዋጋ ሰጣት።