ከዚያም ወደ ዳቤር ሰዎች ሄዱ፤ አስቀድሞም የዳቤር ስም ሀገረ መጻሕፍት ነበረ።
ከዚያም ቀደም ሲል ቂርያትሤፍር ተብላ በምትጠራው በዳቤር በሚኖሩት ሰዎች ላይ ዘመቱ።
ከዚያም ተነሥተው በዳቤር በሚኖሩት ሰዎች ላይ ዘመቱ፤ የዳቤር የቀድሞ ስም ቂርያት ሴፌር ነበር።
ከዚያም የይሁዳ ሰዎች በደቢር ኗሪዎች ላይ ዘመቱ፤ በዚያን ጊዜ ከተማይቱ “ቂርያት ሴፌር” ተብላ ትጠራ ነበር።
ከዚያም የዳቤርን ሰዎች ሊወጋ ሄደ፥ አስቀድሞም የዳቤር ስም ቅርያትሤፍር ነበረ።
ከዚያም ካሌብ በዳቤር ሰዎች ላይ ዘመተ፤ የዳቤርም ስም አስቀድሞ “ሀገረ መጻሕፍት” ነበረ።
ካሌብም፥ “ሀገረ መጻሕፍትን ለሚመታና ለሚይዝ ልጄን ዓስካን ሚስት ትሆነው ዘንድ እሰጠዋለሁ” አለ።