አባቱም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘ያማሩ ልብሶችን ቶሎ አምጡና አልብሱት፤ ለጣቱም ቀለበት፥ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት፤’
ኢያሱ 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግራቸውም ያደረጉት ጫማ ያረጀና ማዘቢያው የተበጣጠሰ፥ ልብሳቸውም በላያቸው ያረጀ ነበረ፤ ለስንቅም የያዙት እንጀራ ሁሉ የደረቀ፥ የሻገተና የተበላሸ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹም ያረጀና የተጠጋገነ ነጠላ ጫማ አድርገዋል፤ አሮጌ ልብስ ለብሰዋል፤ ለስንቅ የያዙት እንጀራም በሙሉ የደረቀና የሻገተ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያረጀና የተጠጋገነ ጫማ በእግራቸው አደረጉ አሮጌም ልብስ ለበሱ፤ ለስንቅም የያዙት እንጀራ ሁሉ የደረቀና የሻገተ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተቀዳዶ ያለቀ አሮጌ ልብስ ለብሰው፥ የተጠጋገነ እላቂ ጫማ አደረጉ፤ ለስንቅ የያዙትም እንጀራ ደረቅና የሻገተ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያረጀ የተጠቀመም ጫማ በእግራቸው አደረጉ አሮጌም ልብስ ለበሱ፥ ለስንቅም የያዙት እንጀራ ሁሉ የደረቀና የሻገተ ነበረ። |
አባቱም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘ያማሩ ልብሶችን ቶሎ አምጡና አልብሱት፤ ለጣቱም ቀለበት፥ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት፤’
ወደ እናንተ ለመምጣት በተነሣንበት ቀን ይህን እንጀራ ትኩሱን ለስንቅ ከቤታችን ያዝነው፤ አሁንም እነሆ፥ ደርቆአል፤ ሻግቶአልም።
እነዚህም የጠጅ ረዋቶች አዲሶች ሳሉ ሞላንባቸው፤ እነሆም፥ አርጅተው ተቀድደዋል፤ መንገዳችንም እጅግ ስለ ራቀብን እነዚህ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችን አርጅተዋል።”
እነርሱ ደግሞ ተንኰል አድርገው መጡ፤ ለራሳቸውም ስንቅ ያዙ፤ በትከሻቸውም ላይ አሮጌ ዓይበትና ያረጀና የተቀደደ የተጠቀመም የጠጅ ረዋት ተሸከሙ።
ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ጉባኤ ወደ ጌልገላ መጥተው ለኢያሱና ለእስራኤል ሁሉ፥ “ከሩቅ ሀገር መጥተናል፤ አሁንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ” አሉ።