La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 9:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢያ​ሱም ጠርቶ፥ “እና​ንተ በመ​ካ​ከ​ላ​ችን የም​ት​ኖሩ ስት​ሆኑ፦ ‘ከእ​ና​ንተ እጅግ የራ​ቅን ነን’ ብላ​ችሁ ለምን አታ​ለ​ላ​ች​ሁን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “እዚሁ አጠገባችን መኖራችሁ የታወቀ ሆኖ ሳለ፣ ‘የምንኖረው ከእናንተ በራቀ ስፍራ ነው’ ብላችሁ ያታለላችሁን ለምንድን ነው?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱም ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ በመካከላችን ስትኖሩ፦ ‘ከእናንተ እጅግ የራቅን ነን’ ብላችሁ ለምን አታለላችሁን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢያሱም የገባዖንን ሕዝብ ወደ እርሱ ፊት እንዲቀርቡ አድርጎ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፤ “በዚሁ በቅርብ የምትኖሩ ሲሆን፥ በጣም ሩቅ ከሆነ አገር የመጣን ነን ብላችሁ ስለምን አታለላችሁን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱም ጠርቶ፦ እናንተ በመካከላችን ስትኖሩ፦ ከእናንተ እጅግ የራቅን ነን ብላችሁ ለምን አታለላችሁን?

Ver Capítulo



ኢያሱ 9:22
9 Referencias Cruzadas  

በነ​ጋም ጊዜ እነሆ ልያ ነበ​ረች፤ ያዕ​ቆ​ብም ላባን፥ “ምነው እን​ደ​ዚህ አደ​ረ​ግ​ህ​ብኝ? ያገ​ለ​ገ​ል​ሁህ ስለ ራሔል አል​ነ​በ​ረ​ምን? ለምን አታ​ለ​ል​ኸኝ?” አለው።


ነገር ግን እባብ ሔዋ​ንን በተ​ን​ኰሉ እን​ዳ​ሳ​ታት፥ አሳ​ባ​ችሁ ከክ​ር​ስ​ቶስ የዋ​ህ​ነ​ትና ንጽ​ሕና ምና​ል​ባት እን​ዳ​ይ​ለ​ወጥ ብዬ እፈ​ራ​ለሁ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ቃል ኪዳን ካደ​ረጉ ከሦ​ስት ቀን በኋላ ከቅ​ርብ እን​ደ​ሆ​ኑና በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰሙ።


በገ​ባ​ዖን የሚ​ኖሩ ሰዎች ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​ያ​ሪ​ኮና በጋይ ያደ​ረ​ገ​ውን በሰሙ ጊዜ፥


ወደ ኢያ​ሱና ወደ እስ​ራ​ኤል ጉባኤ ወደ ጌል​ገላ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ “ከሩቅ ሀገር መጥ​ተ​ናል፤ አሁ​ንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጉ” አሉ።