ኢያሱ 9:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱንና እስራኤልን ሁሉ ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱንና እስራኤልን ለመውጋት በአንድነት መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀይላቸውን በአንድነት አስተባብረው በኢያሱና በእስራኤላውያን ላይ ለመዝመት መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ። |
እንዲህም አለኝ፥ “ይህ ሕዝብ፦ ከባድ ነው የሚለውን ሁሉ፦ ከባድ ነው አትበሉ፤ መፈራታቸውንም አትፍሩ፤ አትደንግጡም።
አምስቱም የኢያቡሴዎን ነገሥት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የላኪስ ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥ ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፤ ከገባዖንም ጋር ሊጋጠሙ ከበቡአት።
ዮርዳኖስንም ተሻገራችሁ፤ ወደ ኢያሪኮም መጣችሁ፤ የኢያሪኮም ሰዎች፥ አሞሬዎናዊው፥ ፌርዜዎናዊው፥ ከነዓናዊው፥ ኬጤዎናዊው፥ ጌርጌሴዎናዊው፥ ኤዌዎናዊው፥ ኢያቡሴዎናዊው ተዋጉአችሁ፥ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋቸው።
ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።